የኢትዮጵያ ግብርና እና የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽኖች በ2011 በጀት ዓመት ብር 112.2 ሚሊዮን አተረፉ
በሆቱልና ቱሪዝም አገልግሎት መስክ የተሰማሩ 3 የልማት ድርጅቶች በ2011 በጀት ዓመት በድምሩ ብር 138.6 ሚሊዮን አተረፉ
ኤጀንሲው በስሩ ያሉ የልማት ተቋማትን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማቸውንና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅታቸውን መገምገም ጀመረ
ትኩረት የተሰጣቸው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የ9 ወራት አፈጻጸም በገንዘብ ሚኒስቴር ተገመገመ
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ብር 29.6 ቢሊዮን አተረፉ
Back

ኤጀንሲው በስሩ ያሉ የልማት ተቋማትን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸማቸውንና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅታቸውን መገምገም ጀመረ

 

የመንገሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በስሩ ያሉ የልማት ተቋማትን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት  ሐምሌ 24 ቀን መገምገም ጀመረ፡፡ በዚሁ በመጀመሪያው የግምገማ ዕለት ጠዋት የብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ እና ከሰዓት በኋላ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸሞችና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅቶች ተገምግመዋል፡፡

የግምገማ መድረኩን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መርተውታል፡፡ የየድርጅቶቹ ቦርድ አመራር ተወካዮች፣ዋና ሥራአስፈጻሚዎች እና የሥራ አመራር አባላት  እንዲሁም ከኤጀንሲው  የማኑፋክቸሪግና ኢነርጂ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች  በግምገማው ላይ ተገኝተዋል፡፡

የየድርጅቶቹ የአፈጻጸም ሪፖርቶች ከቀረቡ በኋላ በግምገማው ወቅት የኦፕሬሽን ግቦች፣የሪፎርም ሥራዎች፣የማህበራዊ ግልጋሎት ድጋፍ፣የፕሮጀክቶች ትግበራ እና የስጋት አስተዳደር /Risk Management/ ትኩረት ተሰጥቷቸው በዝርዝር ታይተዋል፡፡

በግምገማው ወቅት እንደተገለጸው ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ በኦፕሬሽን ረገድ በበጀት ዓመቱ 12,190,077 ሊትር  የአልኮል መጠጥ እና 5,398,848 ሊትር  ንፁህ አልኮል ለማምረት አቅዶ እንደ ቅደም ተከተላቸው 13,500,496 (የዕቅዱን 111 በመቶ ) እና 5,998,613  (የዕቅዱን 111 በመቶ ) ማከናወን ችሏል፡፡ ሽያጭን በተመለከተ በድምሩ ከአልኮል መጠጥ፣ከንጹህ አልኮል ከእሳት አልኮል ብር 750 ሚሊዮን ለማግኘት አቅዶ ብር 850 ሚሊዮን ወይም የእቅዱን 107 በመቶ ተግባራዊ አድርጓል፡፡  ትርፍ ከታክስ በፊት ደግሞ ብር 200,580,000.00  ለማግኘት አቅዶ ብር 233,450,602.13 ወይም ከዕቅዱ በላይ 16 በመቶ አትርፏ፡፡ ምርቱን ለውጭ ገበያ በማቅረብ 202,000 የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት አቅዶ 464,993 የአሜሪካን ዶላር በማግኘት ዕቅዱን በ230 በመቶ አሳክቷል፡፡

በአጠቃላይ ፋብሪካው በ2011 በጀት ዓመት ያስመዘገበው ውጤት ከዕቅዱ በላይ በመሆኑ ቦርዱ፣ ማኔጅመንቱ እና መላው ሠራተኛ ሊመሰገን እንደሚገባው የኤጀንሲው ዋና ዳሬክተር ገልጸው የ2012 በጀት ዓመት ዕቅዱም ይህንን ውጤት እንደመነሻ በመውሰድ ግቦቹ እንዲስተካከሉ እና የተጀመሩ ፕሮጀክቶች እንዲጠናቀቁ መመሪያ ሰጥተው ግምገማው ተጠናቋል፡፡

ከሰዓት በኋላ በተመሳሳይ ሁኔታ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ ዐፈጻጸምና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት የታየ ሲሆን፣ ድርጅቱ በ2011 በጀት ዓመት ብር 345,426,660 ዋጋ ያላቸውን የህትመት ውጤቶች ለማምረት አቅዶ የብር 302,865,318 ዋጋ ያላቸውን የህትመት ውጤቶች ማምረቱ፣ ይህም አፈጻጸም የዕቅዱ 87.68 በመቶ መሆኑ፣በህትመት ውጤቶች ሽያጭ ረገድ ብር 639,679,000 የሽያጭ ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 537,999,487 በማግኘቱ የዕቅዱን 84.1 በመቶ ማከናወኑ እና ከታክስ በፊት ብር 209,500,343 ለማትረፍ አቅዶ ብር 198,559,162 ትርፍ ስለአገኘ የዕቅዱ 95 በመቶ  ማሳካቱ በግምገማው ወቅት ተገልዷል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ የማተሚያ ድርጅቱ አፈጻጸም የሚያበረታታ መሆኑ ተጠቅሶ፣ የደንበኞችን እርካታ የበለጠ ለማሳደግና እየተካሄዱ ያሉ ፕሮጀክቶችን በጊዜያቸው ለማጠናቀቅ በ2012 በጀት ዓመት ዕቅዱ ትኩረት ሰጥቶ እንዲንቀሳቀስ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

 


  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display