በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከታክስ በፊት 8.9 ቢሊዮን ብር አተረፈ
የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከታክስ በፊት ብር 1.71 ቢሊዮን አተረፈ
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 324 ሚሊዮን አተረፈ


.


በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ የልማት ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን አተረፉ

07/10/2019
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ስር የሚገኙ 23 የልማት ድርጅቶች በ2011 በጀት ዓመት ብር 69.5 ቢሊዮን ከታክስ በፊት ለማትረፍ አቅደው በዕቅድ ዘመኑ ማትረፍ የቻሉ 18 ድርጅቶች ብር 52.3 ቢሊዮን ወይም የዕቅዳቸውን 77 በመቶ ማትረፋቸው ተገለጸ፡፡ ይህ የተገለጸው የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገብረ መስቀል መስከረም 22 ቀን 2012 ዓ.ም. በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ የኤጀንሲውንና የተጠሪ የልማት ተቋማቱን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አስመልክተው ለመገናኛ በዙኃን በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከታክስ በፊት 8.9 ቢሊዮን ብር አተረፈ

07/10/2019
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 8.9 ቢሊዮን አተረፈ፡፡ ድርጅቱ ይህን ትርፍ ሊያገኝ የቻለው መንገደኞችንና ዕቃ በአየር ወደ ተለያዩ የዓለማችን አገሮች በማጓጓዝ እና ሌሎች ተጓዳኝ አገልግሎቶችን በመስጠት ብር 114.6 ቢሊዮን ገቢ በማግኘቱ እንደሆነ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መስከረም 20 ቀን 2012 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡ ከአጠቃላይ ገቢው ውስጥ በውጭ ምንዛሪ የተገኘው 3.9 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑም በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 ዕቅድ ዝግጅት ተገመገመ

26/09/2019
የስኳር ኮርፖሬሽን የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደ ስብሰባ ተገመገመ፡፡ የግምገማ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል ሲሆኑ፣ የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራአስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ከኤጀንሲው የግብርናና አግሮኢንዱስትሪ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ከታክስ በፊት ብር 1.71 ቢሊዮን አተረፈ

19/09/2019
የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 1.68 ቢሊዮን ለማትረፍ አቅዶ ብር 1.71 ወይም የዕቅዱን 102 በመቶ አተረፈ፡፡ ድርጅቱ ይህን ትርፍ ሊያገኝ የቻለው ገቢ ዕቃዎችን በባህር በማጓጓዝ፣ በውጭ ሀገር ወደቦች መካከል የጭነት አገልግሎት በመስጠት፣ በመልቲ ሞዳል ወደ አገር ውስጥ ኮነቴይነርና ተሸከርካሪዎችን በመጓጓዝ፣በዩኒሞዳል ገቢ እና ወጪ ዕቃዎችን በማስተላለፍ፣ በአገር ውስጥ ደረቅ ወደቦች ኮንቴይነርና ገቢ ተሸከርካሪዎችን በማስተናገድ እና ወጪ ጭነት በሀገር ውስጥ በማሸግ ብር 17.85 ቢሊዮን (የዕቅዱን 93.07 በመቶ) ገቢ በማግኘቱ እንደሆነ የበጀት ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መስከረም 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 324 ሚሊዮን አተረፈ

21/08/2019
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት ብር 325 ሚሊዮን ለማትረፍ አቅዶ ብር 324 ሚሊዮን ወይም ከዕቅዱ 100.5 በመቶ አተረፈ፡፡ ይህ ትርፍ ከ2010 በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር የ15 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና እና የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽኖች በ2011 በጀት ዓመት ብር 112.2 ሚሊዮን አተረፉ

09/08/2019
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር የሚገኙ የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር 96.1 ሚሊዮን እና የኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ብር15.1 ሚሊዮን በድምሩ ብር112.2 ሚሊዮን በ2011 በጀት ዓመት ከታክስ በፊት አተረፉ፡፡ ይህ የታወቀው የኮርፖሬሽኖቹ የ2011 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ኮርፖሬሽኖቹ ካቀረቧቸው ሪፖርቶች ነው፡፡

  ክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል

 የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር

Web Content Display Web Content Display

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር የክቡር አቶ በየነ ገብረመስቀል መልዕክት

 

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በአዋጅ ቁጥር 1097/2011  መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን እንደገና እንዲዋቀሩ ማድረጉን ተከትሎ በደንብ ቁጥር 445/2011 ተቋቁሟል፡፡ ኤጀንሲው ከቀድሞው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ሚኒስቴር በተለየ መልኩ አዲስ ተልዕኮ ፣ የትኩረት መስክ እና አደረጃጀት እንዲይዝ ተደርጓል፡፡ 

አዲሱን የመንግሥት አስፈጻሚ አካላት አደረጃጀት ተከትሎ የተቋቋመውን የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲን  በዋና ዳይሬክተርነት እንድመራ ትልቅ ኃላፊነት ተሰጥቶኛል፡፡ ኤጀንሲው በሥሩ 22 ተጠሪ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አሉት፡፡

ኤጀንሲው  የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ውጤታማ ፣ ተወዳዳሪና አትራፊ እንዲሆኑ ዘመናዊ የኮርፖሬት አስተዳደርና የኮርፖሬት ፋይናንስ ሥርዓት ዝርጋታ ፣ አመራርና አስተዳደር ክትትል ፣በመንግሥት የልማት ድርጅቶችና አክሲዮን ማህበራት ውስጥ መንግሥት ያለውን የባለቤትነት መብት ማስጠበቅ ፣በመንግሥት ልማት ፖሊሲ እና በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ስምሪት መካከል የሚኖረውን ቅንጅት ማሳለጥ እንዲሁም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር  የመንግሥት የባለቤትነት ፣ የተቆጣጣሪ እና ፖሊሲ አውጪውን አካላት ኃላፊነትና ሚና በለየ መልኩ መተግበሩን ማረጋገጥ ላይ ያተኮሩ ዋና ዋና ዓላማዎችን እንዲያስፈጽም ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ተግባራትና ኃላፊነቶችም በመቋቋሚያ ደንቡ ተገልፀዋል፡፡

ኤጀንሲው እነዚህን ዓላማዎች እና  ኃላፊነቶች ለማሳካትም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከዚህ ቀደም ከነበረው በተሻለ መልኩ ትርፋማነት ላይ አተኩረው እንዲሰሩ በማስቻል በሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ ማድረግ እና የሀገርን ኢኮኖሚ መደገፍ እንዲችሉ ማብቃት ይጠበቅበታል፡፡

የኤጀንሲው ፣ የተጠሪ የልማት ድርጅቶች አመራሮችና ፈጻሚዎች ይህንን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነት  ለመወጣት የመላው የሀገራችን ህዝብ እና የደንበኛና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ ድጋፍ ወሳኝ እንደሆነ አጥብቀን እናምናለን፡፡

በመሆኑም በምንከተለው ግልጽ አሰራር መሰረት የደንበኛና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎና ድጋፍ እንደምናበረታታ እያስታወቅን፣ ለጋራ ዓላማችን ስኬት ለምታደርጉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ክብር እንዳለን እና ትኩረት ሰጥተን ሁልጊዜም ለመሻሻል እንደምንሰራ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

Web Content Display Web Content Display